የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያ ኃይሎች ቅንጅት (ኢዴኃቅ)
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያ ኃይሎች ቅንጅት (ኢዴኃቅ) የተመሠረተው ሚያዝያ 1983 ዓ.ም. የሕወሀት/ኢሕአዴግ ቡድን በአዲስ አበባ ሥልጣን ሊይዝ አንድ ወር ሲቀረው ነበር። የኢትዮጵያን ህልውና ለመጠበቅና ዘረኛ የሆነ አምባገነን አገዛዝን ለመከላከል የተወሰኑ አምስት ድርጅቶች፤ ልዩነታቸውንና የየግላቸውን አቋምና ጥቅም ወደ ጎን አድርገው፤ የሀገር አድን መርሆ በማንገብ ኢዴኃቅን ለመመስረት ችለዋል። የኢዴኃቅ የድጋፍ አካላት በመላው ዓለም በመቋቋም ከፍተኛ አስተዋጽዎ አበርክተዋል። ኢዴኃቅ በርከት ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶችን፤ ስብስቦችን (ፎረሞችን) ግለሰቦችን፤ አሰባስቦ ለማታገል ያደረገው ጥረት፤ የኅብረቱን መሠረት ለማስፋትና እንቅስቃሴውን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽዎ ነበረው። ኢዴኃቅ ኤርትራን ከኢትዮጵያ ለማስገንጠል ለተሰበሰበው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ በብዙ ገጾች በተጠናከረ ታሪካዊ ማስረጃ የተደገፈ ሰነድ በመስጠት ተቃውሞውን አሰመዝግቧል። የፓሪስን ስብሰባና የአዲስ አበባውን የግዮን የእርቅና የሰላም ስብሰባ በማዘጋጀት ላይ በሀገራችን ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መመሥረት፤ ለሰላምና ለእርቅ የሚገባውን ሚና ተጫውቷል።
ኢዴኃቅ በተቋቋመ ማግስት ሁለት መስራች ድርጅቶች አፈንግጠው በመውጣት ወደ ወያኔ ጎራ መሄዳቸው ኢዴኃቅን በመጠኑም ቢሆን የጎዳ ክስተት ነበር። ከመስራች የኢዴኃቅ አባል ድርጅቶች ውስጥ ዋናዎቹ መላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) እና የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) እንደነበሩ ይታወቃል።
ስለ ኢዴኃቅ የተለያዩ ሠነዶች ያላችሁ ትልኩልን ዘንድ ትብብራችሁን እንጠይቃለን።